Official Communication

Urgent Response Info

መጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች (Generic)

Publication Date August 28, 2026
Issuing Authority Governance Office
Notice Level HIGH PRIORITY

ቀን፡ ነሀሴ 22/2018 ዓ/ም

ማስታወቂያ

ለ መጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በመደበኛ ስልጠና (Generic) መርሃ ግብሮች

የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የቅድመ ምረቃ (Undergraduate) ትምህርት ዘርፎች በመደበኛ ስልጠና መርሃ ግብሮች በተፈጥሮ ሳይንስ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ በየዓመቱ የሚያወጣውን ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ መስፈርቱን የሚያሟሉ የግል አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

Program

Enrollment Type

Departments

Undergraduate

Generic

Anaesthesia

Comprehensive Nursing

Human Nutrition

Medical Laboratory Sciences

Medical Radiology Technology

Midwifery

Pediatrics and Child Health Nursing

Pharmacy

Psychiatry Nursing

Surgical Nursing

የማመልከቻ መስፈርቶች፤

  1. በተፈጥሮ ሳይንሰ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ በየዓመቱ የሚያወጣውን ዝቅተኛ የመቁረጫ ነጥብ ማሟላት የሚችሉ፡፡

  2. በተፈጥሮ ሳይንሰ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁ እና የሪሚዲያል ትምህርት ውሰዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያላችሁ፡፡

  3. በዲፕሎማ ተመርቃችሁ ከስልጠና መስኩ ጋር ተዛማጅ የሆነ ወይም በጤና የትምህርት ዘርፎች ሕጋዊ ዕውቅና ካለው የትምህርት ተቋም በ12+2 ተመርቃችሁ ዲፕሎማ ያላችሁ ወይም ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በደረጃ 4 ወይም በ10+3 የተመረቃችሁ እና የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ (COC) ሰርተፊኬት ያላችሁ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር /ከክልል መንግሥታት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኤጀንሲ የሥራና ሥልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ (ዲፕሎማ)፟ እና የደረጃ 4 ሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የምስክር ወረቀት፡፡

 አመልካቾች ማያያዝ የሚጠበቅባቸው መረጃዎች፡

  1. ሙሉ የትምህርት ማስረጃ የ12ኛ ክፍል ላጠናቀቁ ፡ የ8ኛ፣፣ 12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ውይም ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት እንዲሁም ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፡፡

  2. በዲፕሎማ ለሚመዘገቡ ከ8ኛ፣ 10ኛ ወይም 12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ውይም ማጠናቀቂያ (ESLCE / EHEEQC) ሰርተፊኬት እንዲሁም ከ9-10ኛ ወይም 9 -12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ12+2 ዲፕሎማ እና ከቴክኒክና ሙያ ተቋም በደረጃ 4 ወይም በ10+3 እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) እና ስቱደንት ኮፒ።

  3. የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት ማስረጃ፡፡

  4. የማመልከቻ ክፍያ፡ 200 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000488221257 ገቢ በማድረግ የክፍያ ደረሰኝ፡፡

የማመልከቻ ፣ የፈተና መስጫ ጊዜ እና ቦታ

  1. የማመልከቻ ጊዜና ቦታ፡ ከነሀሴ 27- ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት፤ የምዝገባ ቦታ በዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ይሆናል፡፡

  2. የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ፡ የመግቢያ ፈተና በኮሌጁ ግቢ የሚስጥ ሲሆን የፈተና ቀኑን በውስጥ ማስታወቂያ በኮሌጁ ሬጅስትራር የማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከፈተና ቀን በፊት የሚለጠፍ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በኮሌጁ የማህበራዊ ሚዲያዎች መከታተል ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡

  1. የመግቢያ ፈተናውን ያለፉ አመልካቾች በምዝገባ ወቅት ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ኮፒ፣ ሁለት ጉርድ ፎቶ፣ እና የማመልከቻ ክፍያ ደረሰኝ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

  2. በዲፕሎማ ለሚመዘገቡ የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች የ12+2 ዲፕሎማ እና ከቴክኒክና ሙያ ተቋም በደረጃ 4 ወይም በ10+3 ያጠናቀቁበትን የትምህርት ማስረጃ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ በኮሌጁ የፖስታ ሳጥን ቁጥር 3268 በኩል ከምዝገባ ቀን ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  3. የተሟላመረጃያላቀረቡአመልካቾችንየማንቀበልበመሆኑአስፈላጊዶክመንቶችንበጥንቃቄእንዲያሟሉእንመክራለን፡፡

Theme Setting

THEME
HEADER