Official Communication

Urgent Response Info

መጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች (Post Basic)

Publication Date August 28, 2026
Issuing Authority Governance Office
Notice Level HIGH PRIORITY

ቀን፡ ነሀሴ 22/2018 ዓ/ም

ማስታወቂያ

ለ መጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

በመደበኛ በሙያ ማሻሻያ የስራ ላይ ስልጠና (Post Basic)

የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የቅድመ ምረቃ (Undergraduate) ትምህርት ዘርፎች በመደበኛ በሙያ ማሻሻያ የስራ ላይ ስልጠና (Post Basic) መርሃ ግብሮች የመግቢያ መስፈርቱን የሚያሟሉ የግል አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

Program

Enrollment Type

Departments

Undergraduate

Post Basic

Anesthesia

Comprehensive Nursing

Health Informatics

Medical Laboratory Sciences

Medical Radiology Technology

Midwifery

Pediatrics and Child Health Nursing

Pharmacy

Psychiatry Nursing

Surgical Nursing

Emergency and Critical Care Nursing

Family Health

Neonatal Nursing

Operating Theater Nursing

 

የማመልከቻ መስፈርቶች፤

  1. ከስልጠና መስኩ ጋር ተዛማጅ የሆነ ወይም በጤና የትምህርት ዘርፎች ሕጋዊ ዕውቅና ካለው የትምህርት ተቋም በ12+2 ተመርቃችሁ ዲፕሎማ ያላችሁ ወይም ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በደረጃ 4 ወይም በ10+3 የተመረቃችሁ እና የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ (COC) ሰርተፊኬት ያላችሁ፡፡

  2. ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር /ከክልል መንግሥታት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኤጀንሲ የሥራና ሥልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የትምህርት ማስረጃ (ዲፕሎማ)፟፡፡

  3. ከተማ አስተዳደር/ከክልል መንግስታት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኤጀንሲ ወይም በሥራና ሥልጠና ቢሮ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ የደረጃ 4 ሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የምስክር ወረቀት፡፡

  4. ለ12+2 ዲፕሎማ እና ከቴክኒክና ሙያ ተቋም በደረጃ 4 ወይም በ10+3 ላጠናቀቃችሁበት ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ቀድሞ ከተማሩበት ተቋም ማስላክ የምትችሉ።

  5. በጤና መስክ ቢያንስ የሁለት አመት የስራ ልምድ ማቅረብ የምትችሉ፡፡

  6. አመልካቾች የኮሌጅን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አመልካቾች ማቅረብ የሚጠበቅባቸው መረጃዎች፡

  1. ሙሉ የትምህርት ማስረጃ፡ የ8ኛ፣ 10ኛ ወይም 12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ውይም ማጠናቀቂያ (ESLCE / EHEEQC) ሰርተፊኬት እንዲሁም ከ9-10ኛ ወይም 9 -12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፡፡

  2. የ12+2 ዲፕሎማ እና ከቴክኒክና ሙያ ተቋም በደረጃ 4 ወይም በ10+3 እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) እና ስቱደንት ኮፒ።

  3. የማመልከቻ ክፍያ፡ 200 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000488221257 ገቢ በማድረግ የክፍያ ደረሰኝ

  4. የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት ማስረጃ፡፡

የማመልከቻ ፣ የፈተና መስጫ ጊዜ እና ቦታ        

  1. የማመልከቻ ጊዜና ቦታ፡ ከነሀሴ 27- ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት፤ የምዝገባ ቦታ በዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ይሆናል፡፡

  2. የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ፡ የመግቢያ ፈተና በኮሌጁ ግቢ የሚስጥ ሲሆን የፈተና ቀኑን በውስጥ ማስታወቂያ በኮሌጁ ሬጅስትራር የማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከፈተና ቀን በፊት የሚለጠፍ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በኮሌጁ የማህበራዊ ሚዲያዎች መከታተል ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ

  1. የ12+2 ዲፕሎማ እና ከቴክኒክና ሙያ ተቋም በደረጃ 4 ወይም በ10+3 እንዲሁም የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (COC) ማረጋገጥ (Authenticate) ይኖርባቸዋል።

  2. የመግቢያ ፈተናውን ያለፉ አመልካቾች በምዝገባ ወቅት ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ኮፒ፣ ሁለት ጉርድ ፎቶ፣ እና የማመልከቻ ክፍያ ደረሰኝ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

  3. የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች የ12+2 ዲፕሎማ እና ከቴክኒክና ሙያ ተቋም በደረጃ 4 ወይም በ10+3 ያጠናቀቁበትን የትምህርት ማስረጃ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ በኮሌጁ የፖስታ ሳጥን ቁጥር 3268 በኩል ከምዝገባ ቀን ጀምሮ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  4. የተሟላ መረጃ ያላቀረቡ አመልካቾችን የማንቀበል በመሆኑ አስፈላጊ ዶክመንቶችን በጥንቃቄ እንዲያሟሉ እንመክራለን፡፡

Theme Setting

THEME
HEADER